በካርባላ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ በደረሰ ጥቃት የሰው ህይወት አለፈ

  • ቪኦኤ ዜና

ካርባላ

የኢራቅ የፀጥታ ኃይሎች ካርባላ በተባለችው ከተማ በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ሌሊት በከፈቱት ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች ተገድለዋል።

በመንግሥት ላይ የተነሳው ተቃውሞ አምስተኛ ቀኑን በያዘበት በአሁኑ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች መቁሰላቸውን የፀጥታ ባለሥልጣኖች ገልፀዋል።

መንግሥት ከእኩለ ሌሊት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ የሰዓት እላፊ ገደብ ደንግጓል። ተቃዋሚዎቹ ግን ትዕዛዙን ጥሰው ተሰልፈዋል። ትናንት በፖሊሶችና በተቃዋሚዎች መካከል በተካሄደው ግጭት ቢያንስ 3 ሰዎች ተገድለው ከመቶ በላይ ቆስለዋል።

የሀገሪቱን ፕረዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ካቢኔያናቸውን ላቀፉ ከፍተኛ ፖለቲከኞች ይሰጡ የነበሩ ጥቅማጥቅምን ለመሰረዝ በሀገሪቱ ምክር ቤት የተወሰደው ዕርምጃ ተቃውሞውን ሊያረግብ አልቻለም።

ኢራቅ የነዳጅ ዘይት ኃብት ያላት ሀገር ብትሆንም የኢኮኖሚ ማዝገምን፣ ደካማ የመንግሥት አገልግሎቶችን፣ በሀገሪቱ ተስፋፋ የሚባለው ሙስናን በመቃውም ነው የተቃውቅሞ ስልፍ ሲያካሄዱ የሰነበቱት።