ኢራን 60 በመቶው ንጹህ የሆነ ዩራኒየም በማበልጸግ ላይ ነች

FILE - A picture provided by Iran's Atomic Energy Organization shows Iranian Parliament speaker Mohammad Bagher Ghalibaf, left, and head of the Iranian Atomic Organization Ali Akbar Salehi, right, at the Fordo Uranium Conversion Facility, Jan. 28, 2021.

ፎርዶ በተባልው የአገሪቱ ኑክሌር ጣቢያ 60 በመቶ ንጹህ የሆነ ዩራኒየም በማበልጸግ ላይ መሆኗን ኢራን አስታውቃለች። የሃገሪቱ መንግሥታዊ መገናኛ ብዙሃን እንዳሉት ድርጊቱ የተመድ የኑክሌር ተቆጣጣሪ አካል ላወጣው የአቋም መግለጫ ምላሽ ነው።

ለሃገሪቱ የኑክሌር ፕሮግራም ትልቅ እመርታ ነውም ተብሏል።

60 በመቶ ንጹህ ዩራኒየም ማምረት፣ የኑክሌር መሣሪያ ለማምረት ከሚያስፈልገው ደረጃ፣ ማለትም 90 በመቶ ንጹህ ዩራኒየም አንድ ቴክኒካዊ ደረጃ የቀረው ነው መባሉን የአሶሲየትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

የኑክሌር እገዳን የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ኢራን አሁን ያላት በቂ የሆነ የ60 በመቶ ጥራት ያለው ዩራኒየም በማበልጸጓ፣ ቢያንስ አንድ ኑክሌር ቦምብ ለመሥራት ያስችላታል።

ኢራን ቀድሞውንም ናታንዝ በተባለውና በማዕከላዊ ኢራን በሚገኘው የኑክሌር ማበልጸጊያ ጣቢያዋ 60 በመቶ ንጹህ ዩራኒየም በማበልጸግ ላይ ነበረች። ፎርዶ የተሰኘው ጣቢያ የሚገኘው ከመዲናዋ ቴህራን 100 ኪሜ ርቀት ላይ ነው።