የኢራን ምርጫ

  • ቪኦኤ ዜና

ኢራናውያን ዛሬ ዐርብ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሲያካሂዱ ውለዋል። ታዲያ በኮሮናቫይረስ ስርጭት መባባስ እና ዩናይትድ ስቴትስ በጣለቻቸው ማዕቀቦች ኢኮኖሚው በመንኮታኮቱ ምርጫውን ህዝቡ በእጅጉ ደንታ እንዳልሰጠው ተዘግቧል።

ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ሃሳን ሩሃኒ በህገ የሚፈቀደውን ሁለት የሥልጣን ዘመን ያጠናቅቃሉ፥ ብዛት ያላችው ዕጩ ተፎካካሪዎችም ራሳቸውን ከውድድሩ አውጥተዋል ወይም መስፈርቱን አላሙዋላችሁም ተብለው ተሰርዘዋል።

ሁለት አክራሪ አቋም የሚያቀነቅኑ ዕጩዎች ረቡዕ ዕለት ከውድድሩ ወጥተው ድጋፋቸውን መሰል አቋም ላላቸው የሃገሪቱ የፍትህ ዘርፍ ዋና ባለሥልጣን ሰጥተዋል። ሌላው ብቸኛ ተፎካካሪ ለውጥ አራማጁ የቀድሞ የማዕከላዊ ባንክ ገዢው እብዶናስር ሄማቲ ናቸው።

ይሁንና ተንታኞች እንደሚሉት የሚመረጡት የኢራን መንፈሳዊው መሪ እያቶላህ አሊ ኻሚኒ የሚደግፉዋቸው አክራሪ አቋም አራማጁ ኢብራሂም ራሲ ሳይሆኑ አይቀሩም።