ለተፈናቃዮች ቅድሚያ እንደሚሰጡ ጌታቸው ረዳ ቃል ገቡ

Your browser doesn’t support HTML5

ተፈናቃዮችን ፈጥነው እንደሚመልሱ ጌታቸው ረዳ ቃል ገቡ

መቀሌ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ ዛሬ፣ ረቡዕ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።

ተፈናቃዮችን ለመመለስ የሚገባውን ያህል አለመሥራታቸውን ያመኑት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ይቅርታ ጠይቀዋል።

አስተዳደራቸው ለጉዳዩ ቅድሚያ እንደሚሰጥና ሰብአዊ እርዳታም ለማቅረብ ተግቶ እንደሚሠራ ፕሬዚዳንቱ ልሰልፈኞቹ ምላሽ ሲሰጡ ተናግረዋል።

በቀደሙት ቀናትም በሌሎችም የክልሉ ከተሞች ውስጥ ተመሳሳይ ሰልፎች መካሄዳቸውን ሪፖርተራችን ከመቀሌ ዘግቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡