ኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ሚሊየን ተኩል ሰው ተፈናቅሏል

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ሚሊየን ተኩል ሰው ተፈናቅሏል

ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ሦስት ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ የሚጠጋ ቁጥር ያለው ሰው መፈናቀሉን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት /አይኦኤም/ አስታወቀ።

ድርጅቱ ባለፉት ነኀሴና መስከረም ባካሄደው ዳሰሳ ከሁለት ሚሊየን ተኩል በላይ የቀድሞ ተፈናቃዮች ወደየቀዬአቸው መመለሳቸውን ገልጿል።

አሁን ተፈናቅለው ከሚገኙት 64 ከመቶዎቹ ግጭቶችና ሁከት ያባረሯቸው መሆናቸውን ስለ ሪፖርቱ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቃል አቀባይ ኬ ቪራይ አማራ ክልል ውስጥ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት አብዛኛው የክልል አካባቢ በአዲሱ ጥናት አለመካተቱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ተፈናቃዮቹም ተመላሾቹም አሳሳቢ ችግሮች እንዳሉባቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሥልጣን እንጉዳይ መስቀሌ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡