የአምስት ልጆች እናቷ ወ/ሮ ሚልካ ይማም የናይሮቢ ከተማ ነዋሪ ናቸው። በዚህ አደጋ ሕይወቱን ያጣው የ27 ዓመቱ ሲድራክ ጌታቸው ሁለተኛ ልጃቸው ነበር። ልጃቸው ቅዳሜ ዕለት ወደ እርሳቸው እንዲመጣ በቆረጡለት ትኬት በማርፈዱ ምክኒያት ሳይሳፈር ቀርቶ ትኬቱ ለእሁድ እንደተላለፈና በማግሥቱ አደጋው በደረሰበት አይሮፕላን ላይ እንደተሳፈረ ገልፀዋል።
ወ/ሮ ሚሊካ “እግዚያብሔር እኔንም የኢትዮጵያ ሕዝብንም በዚህ ውስጥ አንድ ነገር ሊያስተምረን ነው ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ደጋግመው ይናገራሉ። “ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ይሄ የኔ ነው’ ፣ ‘ያ የኔ ነው’ የምንለውን ነገር በማናስበው ደቂቃ ውስጥ ጥለነው እንሄዳለን። ይሄ ለኛ ትልቅ ማንቂያ ሊሆን ይገባል” ብለዋል።
“እንኳን ብሔር ብሔረሰቦች ቀርቶ ሁላችሁም የዓለም ሕዝቦች ይህችው ናችሁ። ከአፈር አታልፉም በሚል እግዚያብሔር ሊያስተምረ ነው የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ” ይላሉ።
ፍተሻውን ጨርሶ ወደ አይሮፕላን እየገባ መሆኑን የነገራቸውን የልጃቸውን ሁኔታ ያስታወሱት ወ/ሮ ሚልካ “ልጄ እኔን አዋርቶ ከስድስት ደቂቃ በኋላ እዚች ምድር ላይ የለም። እኛም ከዚህ የተለየን ሰዎች አይደለንም።” ብለዋል። ሐዘናቸውን ዋጥ አድርገውም የልጃቸው ሞት በሕይወት ያሉትን አስተሳስቦ በፍቅር የማስተሳሰሪያ ትምሕርት ነው ብለዋል።
(ዝርዝሩን ያዳምጡት)
Your browser doesn’t support HTML5