ሐምሌ 19 ለሥቃይ አያያዝ ወይም ለቶርቸር ሰለባዎች ዓለም ድጋፉን የሚገልፅበት ቀን ነው

ሐምሌ 19 ለሥቃይ አያያዝ ወይም ለቶርቸር ሰለባዎች ዓለም ድጋፉን የሚገልፅበት ቀን ነው

ሐምሌ 19 ለሥቃይ አያያዝ ወይም ለቶርቸር ሰለባዎች ዓለም ድጋፉን የሚገልፅበት ቀን ነው

ይህ የዛሬ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መመሥረቻ ቻርተርና ሰባ ዓመት በሀገሮች መካከል ከተፈረመው የሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ድንጋጌ ጋር የተያያዘ ዕለት ዘንድሮ በዓለም ደረጃ ሲታሰብ ሃያኛ ዓመቱ ነው። ጽዮን ግርማ በኢትዮጵያ በየእሥር ቤቱ ይደርስባቸው የነበሩ የከፉና የሥቃይ አያያዞችን ያካፈሉን ሰሞኑን የተለቀቁ የቀድሞ እሥረኞች ታሪክ ይዛ ተከታዩን ዘገባ አሰናድታለች።

Your browser doesn’t support HTML5

ሐምሌ 19 ለሥቃይ አያያዝ ወይም ለቶርቸር ሰለባዎች ዓለም ድጋፉን የሚገልፅበት ቀን ነው

ለሥቃይ አያያዝ ወይም ለቶርቸር ሰለባዎችና ከሥቃይ ለተረፉ ዓለም ድጋፉን የሚገልፅበት የዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ በ1990 ዓ.ም የታሰበው ዴንማርክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ባሳሰበችውና በአባል ሀገሮች ተቀባይነት በማግኘቱ ነበር።

ቀኑ የተመረጠው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መመሥረቻ ቻርተር በ1937 ዓ.ም. /በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር/ የተፈረመበት፤ እንዲሁም የመንግሥታቱ ድርጅት ቶርቸርና ሌሎችም የጭካኔ፣ ኢሰብዓዊና ሰብዕናን የሚያዋርዱ አያያዞችንና ቅጣቶችን የሚያወግዘው የመንግሥታቱ ድርጅት ስምምነት በ1979 ዓ.ም. /አሁንም በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር/ ተግባራዊ የተደረገበት ዕለት በመሆኑ ነበር።

ስምምነቱን ፈርመው እስከዛሬ በየፓርላማዎቻቸው ያስፀደቁ ሃገሮች ቁጥር 163 የደረሰ ሲሆን ሰነዱን ግንቦት 5 / 1986 የብሄራዊ ሕጎቿ አካል ያደረገችው ኢትዮጵያ ከዚያ በቀደሙ ዓመታትም ሆነ ከዚያ ወዲህ ሰብዓዊ መብቶችን በመጣስ፣ ሰዎችን ኢሰብዓዊ በሆነ፣ በማሰቃየትና ሰብዕናን በሚያዋርድ ሁኔታ በመያዝ በዓለምአቀፍ ተቋማትና በሃገር ውስጥ ተቃዋሚዎች፣ እንዲሁም በመደበኛ ዜጎቿ ስትወቀስ ቆይታለች።

መንግሥቷ ያቋቋመው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድም ይህንኑ የሃገሪቱን የመብቶች ረገጣ ታሪኮች እያረጋገጡ ተናግረዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለእነዚያ ያለፉ ዓመታት የጭካኔና የሥቃይ አድራጎቶች በአደባባይ ይቅርታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል። የመንግሥት የሽብር አድራጎትም ብለው ጠርተውታል።

በየእሥር ቤቱ ይደርስባቸው የነበሩ የከፉና የሥቃይ አያያዞችን ያካፈሉን ሰሞኑን የተለቀቁ የቀድሞ እሥረኞች ነበሩ።

የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን ዕለቱ ታስቦ እንዲውል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተወሰነ ቀን ሲናገሩ ፤“ይህ ዕለት ይፈፀማል ተብሎ ሊታሰብ የማይችል መከራና ሥቃይን ለተቀበሉ ያለንን ክብር የምንገልፅበት ነው። ሊነገር ስለማይቻለው ይናገር ዘንድም ዓለም ዕድሉን የሚያገኝበት ቀን ነው። ይህ በመላው ዓለም ቁጥራቸው ሊገለፅ ለማይችል የሥቃይ ሰለባዎች አክብሮታችንንና ድጋፋችንን የምንገልፅበት ቀን መደንገግ የነበረበት ዛሬ አልነበረም፤ እጅግ አርፍደናል” ብለው ነበር።