ፓኪስታን፣ በአንድ በስለላ በተጠረጠረ ህንዳዊ ዜጋ ላይ ያስተላለፈችውን የሞት ፍርድ እንደገና እንድትመረምር፣ ዓለማቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ጥያቄ መጠየቁ ተገለጸ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በስለላ የተጠረጠሩትና በጡረታ ላይ የነበሩት ህንዳዊው የባሕር ኃይል መኮንን፣ ኩልቡሻን ጃደሃቨ ፓኪስታን ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋሉት እአአ መጋቢት 2016 ዓ ከሦስት ዓመት በፊት መሆኑም ታውቋል።
ህንድ ጃደሃቨ የተጠረጠሩበትን የስለላ ወንጀል ስታስተባብል፣ የቀድሞው የባህር ኃይል መኮንን የታሰሩት፣ ኢራን ውስጥ በግል የንግድ ሥራ ላይ በነበሩት ወቅት ነው ብላለች።
ፓኪስታን የጄኔቫውን ስምምነት መጣሷንም በመጥቀስ፣ ህንድ ማስተባበያዋን አጠናክራለች።