ህንድ ውስጥ የደፈሩና የገደሉ ተለቀቁ

  • ቪኦኤ ዜና
ህንድ ውስጥ አንዲት ሴትን በቡድን በመድፈርና በግድያ ወንጀል ዕድሜ ይፍታህ ተፈርዶባቸው የነበረ አሥራ አንድ ወንዶች መለቀቃቸው በመቃውም የመብት ተሟጋቾችና ተቃዋሚዎች ሰልፍ ወጥተዋል፣ ኒው ዴሊ፣ ህንድ፣ 8/18/ 2022

ህንድ ውስጥ አንዲት ሴትን በቡድን በመድፈርና በግድያ ወንጀል ዕድሜ ይፍታህ ተፈርዶባቸው የነበረ አሥራ አንድ ወንዶች መለቀቃቸው በመቃውም የመብት ተሟጋቾችና ተቃዋሚዎች ሰልፍ ወጥተዋል፣ ኒው ዴሊ፣ ህንድ፣ 8/18/ 2022

ህንድ ውስጥ አንዲት ሴትን በቡድን በመድፈርና በግድያ ወንጀል ዕድሜ ይፍታህ ተፈርዶባቸው የነበረ አሥራ አንድ ወንዶች መለቀቃቸው ተቃውሞ አስነስቷል።

የወንጀለኞቹ መለቀቅ በፍትኅ ሥርዓቱ ላይ ዕምነት እንዳይኖራት ያደረገ መሆኑን የተደፈረችው ተፋራጅ ገልፃ መንግሥት ውሳኔውን እንዲቀለብስ ጠይቃለች።

ጥቃቱ ቢልኪስ ባኖና ቤተሰቧ ላይ የተፈፀመው ከሃያ ዓመታት በፊት ጉጅራት ክፍለግዛት ውስጥ ህይወት የጠፋበት ብጥብጥ በተካሄደበት ወቅት ነበር።

ቢልኪስ በቡድን ሲደፍሯት የአስምት ወር ነፍሰጡር የነበረች ሲሆን የሦስት ዓመት ሴት ልጇንና የቤተሰቧን ሰባት አባላት ገድለውባታል።

ፍርደኞቹ የእሥራት ዘመን ምኅረት እንዲደረግላቸው ያቀረቡትን ማመልከቻ የጉጅራት መንግሥት ተቀብሎ ባለፈው ሰኞ ለቅቋቸዋል።

የእስልምና ዕምነት ተከታይ የሆነችው አሁን በአርባዎቹ ዕድሜዋ ውስጥ ያለችው ቤልኪስ የጉጅራት መንግሥት “ያለፍርሃት በሰላም የመኖር መብቴ እንዲከበር ውሳኔውን ይሠርዝ” ስትል ጠይቃለች።

ጉጅራትን የሚያስተዳድራት የብሄርተኛ ሂንዱዎች ብሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ ነው።