ቀይ መስቀል ሁለተኛ ዙር ቁሳቁስ ለትግራይ አደረሰ

Your browser doesn’t support HTML5

ቀይ መስቀል ሁለተኛ ዙር ቁሳቁስ ለትግራይ አደረሰ

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ለሁለተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ማጓጓዙን አስታወቀ።

ከመስከረም ወር በኋላ እስካሁን ድጋፉን ማድረግ አቋርጦ የነበረው በህክምና ቁሳቁሶች ግብዓት እጥረትና በጸጥታ ሥጋት ጭምር እንደነበርም አመልክቷል።

በአፋርና አማራ ክልሎችም ድጋፎችን እያደረጉ መሆኑንም የዓለም አቀፉ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ፋቲማ ሳኮር ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።