የዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በጦር ወንጀለኛነት የተከሰሱትን የቀድሞ የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት ሎሬንት ግባግቦን ነፃ አላቸው።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በጦር ወንጀለኛነት የተከሰሱትን የቀድሞ የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት ሎሬንት ግባግቦን ነፃ አላቸው። ግባግቦ የተከሰሱት፣ እአአ ከ2010 ምርጫ ጋር ተያይዞ በተቀሰቀሰ አመፅ፣ የጦር ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው ነው።
የግባግቦ ደጋፊዎች፣ የ73 ዓመቱን የቀድሞ ፕሬዚዳንት እንዲሁም የርሳቸውን የቅርብ ረዳትና የቀድሞ የወጣቶች ሚኒስትር ቻርልስ ብሌጎዴን ነፃ ያወጣው የፍርድ ውሳኔ ሲሰማ፣ ደስታቸውን በሆታ ገልፀዋል።
በ2010 ማብቂያና በ2011 መጀመሪያ ላይ በነበረው አመጽ፣ ከ3,000 በላይ ሕዝብ መሞቱ ይታወቃል።