በአፍሪካ ኤችአይቪ/ኤድስን ለመከላከል ለተገኙት ውጤቶች የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ ሊመሰገኑ እንደሚገባ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤድስ ቢሮ ዋና ድሬክተር አስታወቁ።
በአፍሪካ ኤችአይቪ/ኤድስን ለመከላከል የተደረጉ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸውንም የመንግሥታቱ ድርጅት የፀረ-ኤድስ ዘመቻው መርኃግብር ማስተባበሪያ ቢሮ ዋና ዳይሬክተር አመልክተዋል።
በኤድስ እና በአባለ ዘር በሽታዎች ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ትናንት ዕሁድ በአዲስ አበባ ሲከፈት የተናገሩት ዳይሬክተሩ ሚሼል ሲዲቤ ለተገኙት ውጤቶች የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ ሊመሰገኑ እንደሚገባም ተናግረዋል
የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ።