ዛሬ ረቡዕ ፓኪስታን ውስጥ የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ተጠናቆ ድምፅ እየተቆጠረ ነው። ሁከት በቀላቀለው ምርጫ ቢያንስ አንድ መቶ ሥድስት ሚሊዮን ሰው ድምፅ ሰጥቷል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ዛሬ ረቡዕ ፓኪስታን ውስጥ የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ተጠናቆ ድምፅ እየተቆጠረ ነው። ሁከት በቀላቀለው ምርጫ ቢያንስ አንድ መቶ ሥድስት ሚሊዮን ሰው ድምፅ ሰጥቷል።
ድምፅ መስጠቱ በተጀመረ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በደቡባዊ ባሉቺስታን ክፍለ ሃገርዋ ዋና ከተማ ኬታ ኃይለኛ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ ደርሶ ከሰላሳ አንድ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አርባ ሰዎች ቆስለዋል።
ፅንፈኛው እስላማዊ መንግሥት ቡድን ኃላፊነቱን ወስዷል። ከጥቃቱ ሰለባዎች መካከል መራጮች ፖሊሶች እና የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴ መሪዎች እንደሚገኙባቸው ፖሊሶች ተናግረዋል።
ከኢራን ጋር በሚያዋስን የክፍለ ሃገርዋ ኣካባቢ ደግሞ ታጣቂዎች የምርጫ ሰራተኞ እና ፖሊሶች ተከታትለው በሚጓዙባቸው መኪናዎች ላይ ተኩስ ከፍተው ሦስት ሰዎች መግደላቸውን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አስታወቀዋል። በምርጫው ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሻሪፍ ገዚ የቅድሞ ገዢ ፓርቲና በልሪኬት ስፖርት ኮከቡ ኢምራን ኻን የሚመራው የፓኪስታን ቴህሪክ ኢ ኢንሳፍ ፓርቲ በከባድ ፉክክር ተጠምደዋል።