ኬንያውያን በተቃውሞ ሰልፍ ህይወታቸውን ላጡ የተሰናዳ የመታሰቢያ ሙዚቃ ድግስ ታድመዋል

በኬንያ የታክስ ጭማሪ ያስከተለው ተቃውሞ የሀገሪቱ መሪ አወዛጋቢውን ረቂቅ አዋጅ እንዲሰርዙ ማድረጉን ተከትሎ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኬንያውያን እሁድ እለት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የተካሄደውን የመታሰቢያ የሙዚቃ ድግስ ታድመዋል፤ ናይሮቢ፣ ኬንያ፣ እእአ አነሃሴ 7/2024

በኬንያ የታክስ ጭማሪ ያስከተለው ተቃውሞ የሀገሪቱ መሪ አወዛጋቢውን ረቂቅ አዋጅ እንዲሰርዙ ማድረጉን ተከትሎ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኬንያውያን እሁድ እለት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የተካሄደውን የመታሰቢያ የሙዚቃ ድግስ ታድመዋል።

በሃያዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ኬንያውያን ወጣቶች የመሩት ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ሁከት መቀየሩን ተከትሎ 39 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የሰብአዊ መብት ተቋማት ተናግረዋል። አዋጁን እንዲሽሩ የተገደዱት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶም አዲስ መንግሥታቸው ወጪ እንደሚቀንስ ቃል ገብተዋል።

በተቃውሞ ህይወታቸውን ያጡትን ሰዎች ለማሰብ የተሰናዳውን የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም እሁድ እለት ከቀትር በኋላ በርካታ ሰዎች ናይሮቢ በሚገኘው ኡሁሩ ፓርክ ተገኝተዋል። ከነዚህ አንዱ የ29 አመቱ ቪክቶር ዋይታካ፣ በዝግጅቱ ላይ የታደመው ውድቅ በተደረገው የታክስ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ በተነሳው ተቃውሞ ለሞቱት ጀግኖች ክብር ለመስጠት ነው ሲል፣ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግሯል።

ታዳሚዎቹ ባለፉት ሳምንታት ተቃዋሚዎች ያነሱት የነበረውን ጥያቄ በማስተጋባት "ሩቶ መሄድ አለበት" በማለት ድምፃቸውን ሲሆን፣ የተለያዩ ድምፃውያን እና የኪነጥበብ ሰዎች ባቀረቧቸው ዝግጅቶች ሲደንሱ እና የኬንያን ባንዲራ ሲያውለበልቡም ታይተዋል።

ፕሬዝዳንት ተቃውሞውን ተከትሎ አዲስ የብድር እና የወጪ ቅነሳ እቅዶችን ባለፈው ሳምንት አርብ ይፋ ካደረጉ በኃላ ኤክስ በተሰኘው የማህበራው ትስስር ገፅ ላይ ከወጣቶች ጋር ጠንካራ ውይይቶችንም አካሂደዋል።