ለሦርያ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ በተፈለገው ጊዜ ማድረስ አልተቻለም

  • ቪኦኤ ዜና
ዓለማቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የተመድ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ ወደ ምሥራቃዊቷ የሦርያ ከተማ ጉታ የሚሄደውን እርዳታ የጫኑ ካሜዎኖች ዛሬ ዐርብ መንቀሳቀሳቸው ተሰማ፤ ዳሩ ግን በአካባቢው የሚካሄደው የአየር ጥቃት በአስቸኳይ የተፈለገውን እርዳታ ማራገፍ እንዳላስቻለ ታውቋል።

ዓለማቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የተመድ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ ወደ ምሥራቃዊቷ የሦርያ ከተማ ጉታ የሚሄደውን እርዳታ የጫኑ ካሜዎኖች ዛሬ ዐርብ መንቀሳቀሳቸው ተሰማ፤ ዳሩ ግን በአካባቢው የሚካሄደው የአየር ጥቃት በአስቸኳይ የተፈለገውን እርዳታ ማራገፍ እንዳላስቻለ ታውቋል።

በሦርያ የተመድ የአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ አሊ አልዛታሪ በተናገሩት ቃል፣ የአሁኑ ውጊያ የተጀመረው፣ የሩስያውን ፌዴሬሽን ጨምሮ፣ ከወዳጅ ወገኖች የተሰጠው የደኅንነት ዋስትና በመክሸፉ እንደሆነ አመልክተዋል።

ጥቃቱ የተቀሰቀሰው፣ የእርዳታ አቅርቦቱን የጫኑት 13 ኮንቮዮች፣ ባለፈው ሰኞ መድረስ የነበረበትን ጭነታቸውን ለማራገፍ ወደ ዶማ ሲቃረቡ መሆኑ ታውቋል።

በተመድ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ኮሚሽነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን ምሥራቅ ጉታ የሚገኙ ወንጀለኞች ለጥቃቱና ለእርድታው መስተጓጎል ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።