ሰመጉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ዓመታዊ ሪፖርቱን አላወጣም

  • መለስካቸው አምሃ
ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ /ሰመጉ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስገዳጅ ድንጋጌዎች ምክንያት አንዳንድ ሥራዎቹን ለጊዜው ለማቋረጥ መገደዱን ይፋ አደረገ፡፡

ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ /ሰመጉ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስገዳጅ ድንጋጌዎች ምክንያት አንዳንድ ሥራዎቹን ለጊዜው ለማቋረጥ መገደዱን ይፋ አደረገ፡፡ ሌሎቹን ደግሞ ለማስተላለፍና ስፋት እና መጠናቸውን ዝቅ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ፡፡

በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥሰቶችን የመመርመር ሥራውን ግን እንደቀጠለ መሆኑን ገልጿል፡፡ ጉባዔው ታላቅ ባለውለታዎቼ ናቸው ላላቸው አንጋፋ መስራቾቹ እና መሪዎቹ እውቅና ሰጥቷል፡፡

መጋቢት 24/2009 ዓ.ም. ሃያ ስድስተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው የቀደሞው ኢሰመጉ የዛሬው ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ /ሰመጉ/ የሥራ አመራር አካል ያቀረበው ዓመታዊ የሥራ ዘገባ እንደሚያመለክተው መግለጫዎችን ለማውጣት በቂ ሥራዎች የተሠሩ ቢሆንም መደበኛም ሆነ አስቸኳይ መግለጫዎችን ማውጣት አልተቻለም፡፡

ለዚህም በአለፉት ስድሥት ወራት በሀገሪቱ በቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌዎች ምክንያት ነው ሲል ዘገባው ያስረዳል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ሰመጉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ዓመታዊ ሪፖርቱን አላወጣም