Your browser doesn’t support HTML5
ሁለት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሦስት ታዋቂ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን ማገዱን አጥብቀው ተቃወሙ።
አምነስቲና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በተናጥል ባወጧቸው መግለጫዎች፣ በሰብአዊ መብት ዙርያ በሚሠሩ የሲቪል ማኅበራት ላይ የመንግሥት ዛቻና ማስፈራርያ መበርታቱን ተናግረዋል።
አምነስቲ መንግሥት እግዱን እንዲያነሳ ጠይቋል። የማዕከል ዋና ዲሬክተር አቶ ያሬድ ሃይለማርያም፣ ድርጅቶቹ ከመታገዳቸው አስቀድሞም ቢኾን በሰብአዊ መብት ዙርያ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበራትና አመራሮቻቸው ላይ በመንግሥት የጸጥታ አካላት ዛቻና ማስፈራርያ ይደርስ እንደነበር ጠቁመዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ አላገኘንም።