ከታቀደው በላይ የቆዩትን ጠፈርተኞች ለመተካት ሊላክ የነበረው የስፔስ ኤክስ ተልእኮ ዘገየ

በአውሮፓዊያኑ መጋቢት 12. 2025 የተወሰደው ምስል ፣ ኬፕ ካናቭራል ፣ ፍሎሪዳ በሚገኘው የኬኔዲ የጠፈር ማዕከል ለዓለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ ተልዕኮ ዝግጁ የሆነውን የስፔስኤክስ ፋልኮን 9 ሮኬት ከክሬው ድራጎን የጠፈር መንኮራኩር ጋር ያሳያል።

በአውሮፓዊያኑ መጋቢት 12. 2025 የተወሰደው ምስል ፣ ኬፕ ካናቭራል ፣ ፍሎሪዳ በሚገኘው የኬኔዲ የጠፈር ማዕከል ለዓለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ ተልዕኮ ዝግጁ የሆነውን የስፔስኤክስ ፋልኮን 9 ሮኬት ከክሬው ድራጎን የጠፈር መንኮራኩር ጋር ያሳያል።

ጠፈር ላይ ከጊዜያቸው በላይ የቆዩ የ ዩናይትድ ስቴትስ የኤሮኖቲክስ እና ጠፈር ምርምር (ናሳ) ጠፈር ተመራማሪዎችን ለመተካት ወደ ሊላክ የነበረው የስፔስ ኤክስ መንኮራኩር የሮኬት ማስወንጨፊያ እክል ስለገጠመው ወደ ጠፈር ጣቢያው የሚያደርገው በረራ ዘግይቷል፡፡

ቡች ዊልሞር እና ሱኒ ዊሊያምስ የተባሉት ጠፈርተኞች ከዘጠኝ ወራት ቆይታ በኋላ ወደ ምድር ከመመለሳቸው በፊት እነሱን የሚተካ የጠፈርተኞች ቡድን ከዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ መድረስ ይኖርበታል፡፡

ይሁን እንጂ ከኬኔዲ የጠፈር ማእከል ሊወነጨፍ ተዘጋጅቶ የነበረውን ፋልከን ሮኬት እክል ገጥሞታል፡፡

አሶስየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ሮኬቶቹን ደግፈው ከያዙት መሳሪያዎች መካከል አንዱን የሚቆጣጠረው የማስወንጨፊያ ክፍል (የማስነሻ ፓድ) ችግር የገጠመው መኾኑን መሀንዲሶች በመናገራቸው ስፔስ ኤክስ (SpaceX) ተልዕኮውን እንዲያዘገይ ተደርጓል፡፡

ችግሩ የታወቀው ሮኬቱ ከመወንጨፉ ከአራት ሰዐታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሲሆን ተልእኮ ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ የተደረገው ከመወንጨፊያ አንድ ሰዓት ያነሰ ጊዜ ሲቀረው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ስፔስ ኤክስ ተልእኮው እንደገና የሚጀመርበትን ቀን መቸ እንደሚኾን ባይረጋገጥም ቀጣዩ ሙከራ ኅሙስ ምሽት ሊደረግ እንደሚችል ተገልጿል ((ኤፒ)፡፡