Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያ ውስጥ የዜጎች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ግፊት ለማድረግ ታልሞ ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት በቀረበው የሕግ ረቂቅ ቀጣይ ሂደት ዙሪያ የተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባኤ ተንተርሶ የተጠናቀረ ዘገባ በትላንትናው ምሽት አሰምተናል።
ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚታየው ሁኔታ ካልተለወጠ HR-128 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሙሉ ምክር ቤቱ ተመርቶ ሊጸድቅ የሚችል መሆኑን ነበር በምክር ቤቱ የብዙኃኑ ፓርቲ ተጠሪ በተገኙበት በተካሄደው ጋዜጣዊ ጉባኤ የተገለጸው።
በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ተወካይ ከኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልሳቸው በእንቅስቃሴው አብረዋቸው እንደሚሰሩ ከጠቀሷቸው ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን አንዱ ናቸው።
አምሳሉ ካሳው ይባላሉ። የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ግብረ-ኃይል ቃል አቀባይ ናቸው። ስለ ጋዜጣዊ ጉባኤው፥ ስለ ረቂቅ ሕጉ እና በኢትዮጵያ ጉዳይ ከምክር ቤት አባላቱ ጋር ስለሚሩት ሥራ ይወያያሉ።