በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ሁሉን አካታች መንግሥት እንዲመሠረት የሚጠይቀው የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ ረቂቅ ባለፈው መስከረም 18/2010 ዓ.ም. ድምፅ ሊሰጥበት የተወሰነ ቢሆንም፣ መስከረም 22 የሕጉ ረቂቅ በምክር ቤቱ ለውሳኔ ከተያዙ አጀንዳዎች ላይ አንዲነሳ ተደርጓል፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ሁሉን አካታች መንግሥት እንዲመሠረት የሚጠይቀው የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ ረቂቅ ባለፈው መስከረም 18/2010 ዓ.ም. ድምፅ ሊሰጥበት የተወሰነ ቢሆንም፣ መስከረም 22 የሕጉ ረቂቅ በምክር ቤቱ ለውሳኔ ከተያዙ አጀንዳዎች ላይ አንዲነሳ ተደርጓል፡፡
ኤችአር - 128 ድምፅ ሳይሰጥነት ለ30 ቀናት መተላለፉን ያረጋገጡልን የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ምንጮች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እራሱ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ጊዜ እንዲሰጠው በመጠየቁ፣ የምክር ቤት አባላትም ለዚህ ዕድል ለመስጠት ፈልገው ነው ይላሉ፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያኤምባሲ ቃል አቀባይና የሕዝብ ዲፕሎማሲ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ወልዴ ውሳኔው እንዲተላለፍ መንግሥታቸው አልጠየቅም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡
የሕጉ ረቂቅ እንዲፀድቅ ዘመቻ ሲያደርጉ የቆዩ የትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያንን ማኅበረሠብ ተወካዮችና ዓለምቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ግን ኤችአር - 128 በፍጥነት ወደ ምክር ቤቱ አጀንዳ ተመልሶ ድምፅ እንዲሰጥበት ጥሪ እያደረጉ ነው፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
Your browser doesn’t support HTML5