ደሴ እና መቀሌ —
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለነገ፤ ነሐሴ 30 በጠራው ስብሰባ ላይ በራያ፣ ወልቃይትና ወጂራት አካባቢዎች ይደርሳል የሚሉትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዲወያይና የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ ትናንት ምክር ቤቱ አጠገብ ሰልፍ የወጡ ጠይቀዋል። የወጣው ሰው በኮቪድ-19 ምክንያት የተወሰነ እንደነበረም ተገልጿል።
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የተጠየቁት የትግራይ ክልል የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ የወልቃይትና የራያ ህዝብ የራሳቸውን እድል በራሳቸው እንዲወስኑ በትግላቸው ያረጋገጡት የትግራይ ምርጫ ለመረበሽ በጣም ጥቂት በብር የተገዙ ሰዎች ያካሄዱት በማለት አጣጥለውታል።
ወይዘሮ ሊያ "በክልሉ የሰብአዊ መብት ጥሰት አለ የተባለው ከሓቅ የራቀና ለህዝብ ንቀት ያላቸው እኛ እናውቅላሃለን በማለት ረብሻ ለመፍጠር በማሴር ነው እንዲህ የሚሉት" ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5