የለገጣፎ ነዋሪዎች አቤቱታና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ምላሽ

ለገጣፎ

ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ ኦሮምያ ክልል ውስጥ በሚገኘው ለገጣፎ አካባቢ ከአርሶ አደር ላይ መሬት ገዝተው የገነቡት ቤት “ሕገወጥ ነው” በሚል እንዲፈርስ መደረጉ “በአደባባይ የተፈፀመብን በደል ነው” ሲሉ ነዋሪዎች እየገለፁ ናቸው።

የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ ደግሞ “ከገበሬ ላይ መሬት መግዛት በራሱ ሕገወጥነት ነው” ብለዋል ለቪኦኤ።የክልሉ መንግሥት ለገጣፎ ብቻ ሳይሆን በመላ ኦሮሚያ ‘በሕገወጥ መንገድ ተሠርተዋል’ የሚላቸውን ግንባታዎች በሙሉ የማፍረስ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

Your browser doesn’t support HTML5

የለገጣፎ ነዋሪዎች አቤቱታና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ምላሽ