በደቡብ አፍሪካ አዲስ ዓይነት የቅድመ-ሰው ዝርያ ቅሪተ-አካል ተገኘ

  • ቪኦኤ ዜና
የሰው ልጅ ምንጭ የተባለ ዝርያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ ዛሬ፤ ጳጉሜ 05/2007 ዓ.ም ይፋ ሆኗል፡፡

Fossils of a newly discovered ancient species, named "Homo naledi", are pictured during their unveiling outside Johannesburg, Sept. 10, 2015.

የሰው ልጅ ምንጭ የተባለ ዝርያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ ዛሬ፤ ጳጉሜ 05/2007 ዓ.ም ይፋ ሆኗል፡፡

የግኝታቸውንና የምርምራቸውን ሪፖርት ኢላይፍ መፅሔት ላይ ያወጡትና ጆሃንስበርግ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ሳይንቲስቶች የዝርያውን ስም “ኦሞ ናሌዲ - Homo Naledi” ሲሉ ጠርተውታል፡፡

homo naledi

ክሬድል ኦፍ ሂዩማንካይንድ እየተባለ በሚጠራው የዓለም ጥብቅ ውርስ አካባቢ ከደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ ወጣ ብሎ በሚገኙ የራይዚንግ ስታር አካባቢ ተያያዥ ዋሻዎች ውስጥ ነው ቅሪተ-አካሉ የተገኙት፡፡

የጋውተንግ ጠቅላይ ግዛት የአስተዳደር ምክር ቤቱ አባል ሌቦንግ ማይሌ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ለሣይንስና ለግኝቶች፣ ለታሪክና ለዕውቀት፤ ታላቅ ቀን ነው” ብለውታል፡፡

ዝርያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኙት ከእነ ሉሲ ዓይነቱ ዝርያ የተለየ መሆኑ ቢገለፅም ዕድሜው ስንት እንደሆነ ግን ገና አልታወቀም፡፡

ለተጨማሪ ከታች ያለውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ
http://www.voanews.com/content/researchers-claim-find-of-early-human-ancestor/2955122.html