Your browser doesn’t support HTML5
ዘመን የጠገቡት የባሕል መድሃኒቶች እና የቤት ውስጥ ሕክምና ዘዴዎች አብላጫ ቁጥር ያለው የማኅበረሰብ ክፍል ሲገለገልባቸው የኖሩ የመሆናቸውን ያህል ጠቀሜታቸው እያደር በዘመናዊ ሳይንስ እየተለየ እና ፋይዳቸውም እየጎላ መምጣቱ ይታወቃል። በአንጻሩም “ለመሆኑ የትኞቹ የባሕል መድሃኒቶች እና የቤት ውስጥ ሕክምና ዘዴዎች መድሃኒቶች ለየትኛው የሕመም ዓይነት ሕክምና ይረዳሉ? በሃኪም የታዘዙ መድሃኒቶችን በምንወስድበት እና በትይዩው የባሕል ሕክምና ስንጠቀም አለያም ከምናዘወትራቸው የምግብ አይነቶች የትኞቹን ስንመገብ በተለይ ማጤን ያሉብን ጉዳዮች ምንድ ናቸው?” የሚሉት ሳምንታዊው ‘ሃኪምዎን ይጠይቁ’ ለምሽቱ ትኩረት ያደረገባቸው ጭብጦች ናቸው።
ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን በዩናይትድ ስቴትሱ የምግብ እና የመድሃኒቶች ቁጥጥር ባለ ሥልጣን በምርምር ባለሞያነት በማገልገል ላይ የሚገኙት ዶ/ር አሌክስ አካሉ ናቸው።