ሂላሪ ክሊንተን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመሥራት ቃል ገቡ

ሂላሪ ክሊንተን የምርጫ ውጤቱን አስመልክቶ ንግግር ሲያደርጉ

ዴሞክራትዋ ዕጩ ፕሬዚዳንት ሂላሪ ክሊንተን እጅግ አስደንጋጭ በሆኑ ቁጥር በቢሊዩነሩ ነጋዴ ዶናልድ ትራምፕ ድል ተመተዋል፡፡

ከጥቂት ሰዓታት በፊት የምርጫውን ውጤት በመቀበል ባሰሙት ንግግርም ደጋፊዎቻቸውን አመስግነው ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር አብረው ለመሥራት ቃል ገብተዋል፡፡

ይህ በርግጥ ቀላል ስሜት የሚያሳድር አይደለም፤ ሲሉ ያልተጠበቀውን ውጤት ለመቀበል የቱን ያህል እንደተቸገሩ በማመልከት የጀመሩት የዴሞክራቷ ዕጩ ሂላሪ ክሊንተን

ሂላሪ ክሊንተን

"በጥርጣሬና በአሉታዊ ሥሜት አንሞላ ልባችንንም እንክፈት" ብለዋል፡፡

እጅግ ከፋፋይነት የታየበት የምርጫ ዘመቻ ያስታወሱት ክሊንተን

"ዛሬ መሪያችን ይሆኑ ዘንድ ዕድል ልንሠጣቸው ይገባል" ሲሉ ለትናንቱ ተፎካካሪያቸው ድጋፋቸውን ለግሠዋል፡፡

ዝርዝሩን አሉላ ከበደ ያቀርበዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ሂላሪ ክሊንተን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመሥራት ቃል ገቡ