ከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መግቢያ ውጤት መስፈርት ቅሬታ አስነስቷል

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፦ ደሴ ከተማ ከጦርነቱ በኋላ

ፎቶ ፋይል፦ ደሴ ከተማ ከጦርነቱ በኋላ

“በቅርቡ የተወሰነው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት መስፈርት በተለይ በምስራቃዊ የአማራ አካባቢዎች የተከሰተውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም” ሲሉ መሰረታቸውን ደሴ ላይ ያደረጉ 15 የሃይማኖትና የሲቪል ድርጅቶች አስታወቁ፡፡

ድርጅቶቹ በተማሪዎችና በአካባቢው ላይ ሊደርስ የሚችለውን ሥነ ልቦናዊ ጉዳትና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ግምት ውስጥ በማስገባት የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ማስተካከያ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ከደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ከዋግ ኅምራና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞኖች እንዲሁም ከደሴ ከተማ አስተዳደር ደረሰኝ ያለውን መረጃ መሰረት ያደረገው የደቡብ ወሎ ዞን መምህራን ማህበር በበኩሉ የ12ኛ ከፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያገኙት ከ25 በመቶ አይበልጡም ብሏል፡፡

የትምሕርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ሳሙሌል ክፍሌ ለተነሱት ቅሬታዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መግቢያ ውጤት መስፈርት ቅሬታ አስነስቷል