የሰሜን ኮርያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ቤይጂንግን ጎበኙ

  • ቪኦኤ ዜና

A limousine without car plates and bearing a gold color emblem on its side arrives amid heavy security at the train station in Beijing, March 27, 2018.

ወደ ቻይና የተጓዘ አንድ የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ቤይጂንግን ለአጭር ጊዜ ጎበኘ፤ ይህም፣ ተነጥለው የሚገኙት የአገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ከቻይና ባለሥልጣናት ጋር ዋና ከተማዋ ውስጥ እንደተገናኙ ጥርጣሬን አስነስቷል።

ወደ ቻይና የተጓዘ አንድ የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ቤይጂንግን ለአጭር ጊዜ ጎበኘ፤ ይህም፣ ተነጥለው የሚገኙት የአገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ከቻይና ባለሥልጣናት ጋር ዋና ከተማዋ ውስጥ እንደተገናኙ ጥርጣሬን አስነስቷል።

የዜና አውታሮች እንደዘገቡት፣ የሰሜን ኮሪያን የልዑካን ቡድን አባላት የጫነው ባቡር፣ ዛሬ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ ባለበት ሁኔታ ከቤይጂንግ ሲነሳ ታይቷል። ውስጡ እነማን እንዳሉ ግን በርግጥ የታወቀ ነገር የለም።

የሰሜን ኮሪያውን ባለሥልጣን ማንነት ለማወቅ ያለው ጥርጣሬ የተጀመረው ሰኞውኑ ሲሆን፣ ያም ፍንጭ የተገኘው ከጃፓን ቴሌቪዥል በታየ ምስል እንደሆነ ተነግሯል።

ለማንኝውም የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናት ይህን መሰል ያልተለመደ ጉብኝት ወደ ቻይና አድርገው እንደማያውቁ አንድ ተንታኝ አስታውቀዋል።