የአቶ ሃብታሙ አያሌውና የአቶ አብርሃም ሰሎሞን መለቀቅ ታገደ

  • መለስካቸው አምሃ

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

Your browser doesn’t support HTML5

የአቶ ሃብታሙ የአቶ አብርሃም ሰሎሞን መለቀቅ ታገደ

የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአመራር አባል የነበሩት አቶ ሃብታሙ አያሌውና ሰባተኛ ተከሣሽ አቶ አብርሃም ሰሎሞን እንዲፈቱ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ አግዷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ውሣኔውን የሰጠው የአቃቤ ሕግን አቤቱታ ተቀብሎ ነው፡፡

ጉዳዩ ያስቀርብ ወይም አያስቀርብ እንደሆነ ለማየትም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በተያያዘ ዜና ቀድሞ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ማሙሸት አማረን የፌደራሉ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በነፃ አሰናብቷቸዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡