ሥራ አቋርጠው የነበሩ የህክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች ወደ ሥራ መመለሳቸውን ገለጹ

ባህር ዳር፣ ኢትዮጵያ

Your browser doesn’t support HTML5

ሥራ አቋርጠው የነበሩ የህክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች ወደ ሥራ መመለሳቸውን ገለጹ

በታጠቁ ዘራፊዎች ምክኒያት የደኅንነት ስጋት ስለገባቸው ባለፈው ሳምንት ሰኞ ሥራ ማቆማቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸው የነበሩ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የህክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች ሙሉ ለሙሉ ወደ መደበኛ ሥራቸውን ከተመለሱ አንድ ሳምንት እደኾናቸው ገለጹ።

ከዩኒቨርስቲውና ከኮሌጁ አመራሮች ጋራ በተደረገ ውይይት የሆስፒታሉን ጥበቃ ለማጠናከር ስምምነት ላይ በመደረሱ ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ከሆስፒታሉ አመራሮች ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።