በጅማ የተፈናቃዮች መጠለያ በተከሰተ በሽታ የሰው ህይወት አለፈ

በጅማ የተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ ሰሞኑን በተከሰተ በሽታ ሕይወት ማለፉን አንዳንድ የመጠለያው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የከተማው መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በመጠለያው መገኘቱን ኩፍኝ አስታውቶ በበሽታው አንድ ህፃን መሞቱን ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ከህመሙ ጋር ተያያዥ ባልሆነ አጋጣሚ ማለፉን ለቪኦኤ ገልጿል።

የኦሮሚያ ጤና ቢሮ በበኩሉ ይህን ችግር የሚያጣራ የቴክኒክ ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ሥፍራው መላኩን አስታውቋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በጅማ የተፈናቃዮች መጠለያ በተከሰተ በሽታ የሰው ህይወት አለፈ