Your browser doesn’t support HTML5
በሲዳማ ክልል፣ ሀዋሳ ከተማ፣በየወሩ ያጋጥማል ያሉት የነዳጅ እጥረት እንዳማረራቸው አሽከርካሪዎችና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።
ችግሩ፣ከአንድ ዓመት ለበለጠ ጊዜ፣ በየወሩ እየተከሰተ መቀጠሉን የጠቀሱት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ ኑሮአቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የሲዳማ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ እጥረቱ የተከሰተው አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ማደያዎች አስር ብቻ በመኾናቸውና በህገ ወጥ ግብይት ምክንያት ነው ብሏል።
በህገ ወጥ ግብይት ተሳተፉ ባላቸው 16 መኪናዎችና አራት ማደያዎች እንደዚሁም 62 ሞተሮችና ባጃጆች ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉንም አመልክቷል።