ሀዋሳ —
ባልተፈለገ እርግዝና፥ በባህልና ባለባቸው የአካል ጉዳትና አዕምሮ ዕድገት ውስንነት ምክንያት በወላጆቻቸው የተጣሉና በማኅበረሰቡ የተገፉ 88 ህፃናትን ከተጣሉበት አንስቶ የሚያሳድግ አንድ የቤተሰብ በጎ አድራጊ ማኅበር መንግሥት ማድረግ የሚገባውን ድጋፍ ባለማድረጉ ሊበተን መሆኑን ማኅበሩ ለቪኦኤ ተናገረ።
የማኅበሩ መስራችና ሰብሳቢ አቶ አርጋው አየለ ማኅበሩ ድጋፍ በማፈላለግ ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት ለ38ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ማካሄዱንና ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ድጋፉን ወደ ኮሮና መከላከል በማዞር 3.4ሚሊዮን በሚገመት ብር የመከላከያ ቁሳቁሶችን ገዝቶ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5