የሐረሪ ክልል 300 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የሐረሪ ክልል 300 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

የሐረሪ ክልል መንግሥት ከህወሃትና “ኦነግ ሸኔ” ጋር ግንኙነት አላቸው ብሎ የጠረጠራቸውን ከ300 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

የክልሉ አቃቤ ሕግ ተጠርጣሪዎቹ ጥቆማ ስለቀረበባቸው ብቻ የተያዙ ሳይሆኑ ለጥርጣሬ መነሻ የሆኑ ተጨማሪ ማስረጃዎች የተገኘባቸው ናቸው ብሏል።

በብሔር ማንነታቸው ተይዘዋል የሚለውን ክስም ትክክል አይደለም ብሎታል።