በድርቅ ምክንያት ከሀረርጌ ተፈናቅለው ሆሮ ጉዱሩ ዞን ሀሙሩ ወረዳ የሰፈሩ ቪኦኤ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች ድጋፍ ቢደረግልንም ችግራችንን በዘላቂነት የሚፈታ ምቹ የግብርና መሬት እንዲሰጠን እንፈልጋለን አሉ::
ነቀምት —
የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ቅሬታው ተገቢ መሆኑን ገልፀው በዞኑ ሌላ ምቹ ቦታ ተፈልጎ እንዲሰፍሩ አልያም ሌላ ቦታ እንዲሄዱ አቅጣጫ ተቀምጧል ሲሉ ለቪኦኤ ገልፀዋል::
የኦሮምያ ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ኃብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ በበኩላቸው በ2012 ዓ.ም. ዕልባት እንዲሰጠው ይሰራል ብለዋል::
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5