ለወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው የምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ መምህራን ሥራ አቆሙ

Your browser doesn’t support HTML5

ለወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው የምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ መምህራን ሥራ አቆሙ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሐዲያ ዞን ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ፣ ለተከታታይ ሦስት ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጹ ከ1ሺሕ600 በላይ የ45 ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ ሥራ ማቆማቸውን አስታወቁ።

አማራጭ ገቢ እንደሌላቸው የገለጹት መምህራኑ፣ ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር እንደተሳናቸውና ለረኀብ እንደተጋለጡ አመልክተዋል። በወረዳውም፣ የ2016 ዓ.ም. የትምህርት መርሐ ግብር እስከ አሁን እንዳልተጀመረ፣ መምህራኑ አክለው ተናግረዋል።

የሐዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ፣ መምህራኑ ለተከታታይ ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው አምነው፣ ችግሩ በበጀት እጥረት እንደተፈጠረና ለመፍታትም ጥረት እየተደረገ እንደኾነ አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።