"የያዝነው የ2023 ሐምሌ ወር፣ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የተመዘገበ፣ ሞቃቱ ወር ነው፤" ሲሉ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ፣ ዛሬ አስታውቀዋል።
ዋና ጸሐፊው፥ “ዛሬ የሰው ልጅ፣ የጋለ መቀመጫ ላይ ተቀምጧል፤” ሲሉ፣ በዘይቤ ገልጸውታል - የሰው ልጅ ጉዳዩን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉበት ለመጠቆም፡፡
የዓለም ሜትሪዮሎጂ ድርጅትንና የአውሮፓ የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽንን መረጃ ጠቅሰው የተናገሩት ጉተሬዥ፣ “በማያሻማ” ኹኔታ ሙቀቱን የፈጠረው፣ የሰው ልጅ ያደረገው እንቅስቃሴ ነው፤ ሲሉ አክለዋል።
የዓለም መሪዎች፣ የሙቀት መጠን መጨመርን ለመግታት በሚደረገው ጥረት፣ የአመራር ድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።