በእስር ላይ የሚገኙ ቀሪ ፖለቲከኞች እየተፈረደባቸው መሆኑን ጠበቆቻቸው ገለጹ

  • ቪኦኤ ዜና
በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ላይ በሽብር ወንጀል ከነበሩት 22 ሰዎች ውስጥ ከክስ ነፃ ወይንም ክስ ተቋርጦ ሀያ አንድ ሲለቀቁ መምህር ደረጀ መርጋ ሳይለቀቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ላይ በሽብር ወንጀል ከነበሩት 22 ሰዎች ውስጥ ከክስ ነፃ ወይንም ክስ ተቋርጦ ሀያ አንድ ሲለቀቁ መምህር ደረጀ መርጋ ሳይለቀቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የወጣት ሊግ አባል የሆነው መምህር ደረጃ መርጋ ከአንድ ሳምንት በፊት ፍ/ቤት በቀረበበት ወቅት ችሎትን በመዳፈር ተብሎ የ7 ወር እሥታር ተፈርዶበት ነበር፡፡

በትናንትናው ዕለት ለቀጠሮ በቀረበበት ወቅት በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ላይ በቀረበበት ክስ እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በአራት ዓመት እሥራት እንዲቀጣ ፈርዶበታል፡፡

መምህር ደረጀ የቂሊንጦ እስር ቤት መቃጠል ጋር በተያያዘም ከሌሎች 37 ሰዎች ጋር ፍርድ ቤት እየተመላለሰ መሆኑን ጠበቃው አቶ ወንድሙ ኢብሳ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል የድሬዳዋ ከተማ ተወላጅ የሆነው አቶ ቱጂ ባሬንቶ በቀረበበት የሽብር ወንጀል የ 11 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል፡፡ በተጨማሪም ችሎት በመድፈር ወንጀል 7 ወር ተፈርዶበታል፡፡