ለጉራጌ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ ታሳሪዎች የተፋጠነ ፍትሕ እንዲሰጥ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ለጉራጌ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ ታሳሪዎች የተፋጠነ ፍትሕ እንዲሰጥ ተጠየቀ

በደቡብ ክልል ከጉራጌ የክልልነት እና ከመጠጥ ውኃ አገልግሎት ጥያቄ ጋራ በተያያዘ በተፈጠረው ሁከት እጃቸው አለበት፤ በሚል፣ በክልሉ ፖሊስ ከ\የታሰሩ ግለሰቦች የተፋጠነ ፍትሕ እንዲሰጣቸው ጠበቃቸው ጠየቁ። እስካኹን 15 እስረኞች በዋስ መፈታታቸውን ፣ ከጠበቆቻቸው አንዱ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ደንበኞቻቸው ተደጋጋሚ ጊዜ ቀጠሮ እየተፈቀደባቸው አላግባብ ለእንግልት መዳረጋቸውን የጠቀሱት ጠበቃው፣ በሒደቱ መጓተት ፖሊስንና ዐቃቤ ሕግን ወቅሰዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዓለማየሁ ማሞ በበኩላቸው፣ ፖሊስ ምርምራውን በማጠናቀቅ ላይ መኾኑን ገልጸው፣ በቅርቡ ክሥ እንደሚመሠረትባቸው አስታውቀዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።