በኢራን ታጣቂዎች ጥቃት የፖሊስ መኮንኖች እና ወታደሮች ተገደሉ

የኢራን ካርታ

የኢራን ካርታ

በኢራን በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት፡ ታጣቂዎች 11 ሰዎችን ገድለው 8 ሰዎችን ማቁሰላቸውን መንግስታዊው የዜና አገልግሎት ዘገበ።

የኢራን መንግስት ቲቪ እንዘገበው የተገንጣይ ቡድን አባላት ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ታጣዎች ደቡብ ምስራቅ ኢራን ውስጥ በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ ለሊቱን ባደረሱት ጥቃት 11 ሰዎችን ገድለው በርካቶች አቁስለዋል። የሲስታን እና የባልቼስታን ግዛት ምክትል አስተዳዳሪ ሲናገሩ ከቴህራን በስተደቡብ ምዕራብ 1408 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው ራስክ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች እና ወታደሮች ተገድለዋል።

ፖሊስ ከጥቃቱ ፈጻሚዎች በርካቶቹን መግደሉን ተናግሯል። መንግስታዊው የዜና ወኪል አክሎም “ጃኢሽ አል-አድል” የተባለውን ተገንጣይ ቡድን ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርጓል። ቡድኑ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2019 ሃያ ሰባት የኢራኑ አብዮታዊ ዘብ አባላት ለገደሉበት የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ኃላፊነቱን ወስዷል። ባለፉት የቅርብ ወራት ውስጥ ታጣቂዎች እና አነስተኛ ተገንጣይ

ቡድኖች መንግስቱን ለመዋጋት በፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ማድረስ የመሳሰሉ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ ተስተውለዋል።