በናይጄሪያ 280 ተማሪዎች ታገቱ

ታጣቂዎች በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ የሚገኝን አንድ ትምህርት ቤት ወረው 280 ተማሪዎችን አግተው መውሰዳቸውን መምህራን እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ለቤዛ የሚፈፀም ጠለፋ የተለመደ ሲሆን፣ ወሮበሎች ትምሕርት ቤቶችን እና ኮሌጆችን ኢላማ እንደሚያደርጉ ታውቋል። ትናንት የተፈጸመው ጠለፋ እስካሁን ከታዩት የከፉ ጠለፋዎች አንዱ እንደሆነ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ጠላፊዎቹ በትምህርት ቤቱ በመግባት ወደ ሰማይ ሲተኩሱ የተወሰኑ ተማሪዎችን ይዘው እንዳመለጡ አንድ መምህር ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።287 ተማሪዎች የተጠለፉ መሆኑን መምህሩ ቢናገሩም፣ የአካባቢው ባለሥልጣት ግን የተማሪዎቹን ቁጥር ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

የተማሪዎቹን ትክክለኛ ቁጥር በተመለከተ አሁንም በማጣራት ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት በመናገር ላይ ናቸው። የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኒቡ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጦራቸውን ልከዋል።

ባለፈው ሳምንት በሰሜን ናይጄሪያ በአንድ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በተፈጸመ ጠለፋ 100 የሚሆኑ ሴቶች እና ሕጻናት በነውጠኞች መወሰደቻውን ዜና አገልግሎቱ ጨምሮ አስታውሷል።