ሀዋሳ —
ከደቡብ ክልል ዲላ ከተማ የኦሮሚያ ክልልን አቋርጠው ወደ አማሮ ልዩ ወረዳ ሲጓጓዙ በነበሩ አምስት የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲያመሩ ላይ በተከፈተ ተኩስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ፣ ሌሎች አራት ሰዎች መቁሰላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ ግለሰቦች እና የአከባቢዎቹ ባለሥልጣት ለአሜሪክ ድምፅ ገለፁ።
ጥቃቱ የተፈፀመበት ምዕራብ ጉጂ ዞን የገላና ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ ጥቃት አድራሾች "ኦነግ ሽኔ" የሚሏቸው የታጠቁ ቡድኖች መሆናቸውን ገልጿል ።
በኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባርነት የተፈረጀው እና መንግሥት “ኦነግ ሽኔ” የሚጠራቸው እራሳቸውን ደግሞ "የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት" ብለው ከሚጠሩት ታጣቂ ቡድኖች መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
በሌላ በኩል የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ አቶ ኦዳ ተርቢ በትዊተር ገፃቸው ላይ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ መንግሥትን ተጠያቂ አድርገዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5