በጉጂ አዳጊ ወንድ ልጃቸው የመከላከያ ሠራዊት አባል ነው በተባለ ሰው እንደተደፈረባቸው አንድ እናት ገለጹ - ፖሊስ ጉዳዩ ምርመራ ላይ ነው ብሏል

Your browser doesn’t support HTML5

በጉጂ አዳጊ ወንድ ልጃቸው የመከላከያ ሠራዊት አባል ነው በተባለ ሰው እንደተደፈረባቸው አንድ እናት ገለጹ - ፖሊስ ጉዳዩ ምርመራ ላይ ነው ብሏል

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ዋደራ ወረዳ፣ የአምስት ዓመት አዳጊ ልጃቸው የመከላከያ ሠራዊት አባል ነው በተባለ ሰው መደፈሩን የልጁ እናት ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። የአዳጊው እናት ድርጊቱ ኅዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በልጃቸው ላይ እንደረፈጸመ ገልጸው፣ አሁን ልጃቸው ሕክምና እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል።

የወረዳው ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተደረገ መኾኑን አስታውቋል። ተጠርጣሪውም በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዳጊው እናት ተናግረዋል።