ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ የተካሄደ የአደባባይ ዝግጅት መሆኑ ተገለፀ

  • እስክንድር ፍሬው

16ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

መጀመሪያ ፍርሃት የነበረ ቢሆንም 16ኛው ታላቁ ሩጫ ውድድር በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ኃይሌ ገ/ሥላሴ አስታወቀ፡፡

42 ሺሕ ሰዎች የተሳተፉበት ይሕ ውድድር በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላ የተካሄደ የመጀመሪያው ትልቅ የአደባባይ ዝግጅት ሆኗል፡፡

"የተለያየ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ልዩነታቸውን አቻችለው በአንድነት ሮጠዋል" ሲል የውድድሩ መስራችና ዳይሬክተር ኃይሌ ገ/ሥላሴ ገለፀ፡፡

16ኛው ታላቁ ሩጫ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ16 ዓመታት፣ ለ16 ጊዜ የተካሄደ የአደባባይ ትዕይንት ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በተለይ የዘንድሮው በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ምክንያት ላይካሄድ እንደሚችል የብዙዎች ጥርጣሬ ነበር፡፡ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም እንዲህ ዓይነት ዝግጅት ሰለመፍቀዱ እርግጠኛ ያልሆኑ ስጋት የገባቸው አልጠፉም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ የተካሄደ የአደባባይ ዝግጅት መሆኑ ተገለፀ