በአከራካሪ አዋሳኝ አካባቢዎች አስተዳደራዊ መዋቅር ለመመሥረት ተወሰነ

Your browser doesn’t support HTML5

በአከራካሪ አዋሳኝ አካባቢዎች አስተዳደራዊ መዋቅር ለመመሥረት ተወሰነ

በትግራይ እና በዐማራ ክልሎች መካከል የይገባኛል ጥያቄ በሚነሣባቸው አዋሳኝ አካባቢዎች፣ አስተዳደራዊ መዋቅር በአስቸኳይ ለመመሥረት አቅጣጫ መቀመጡን፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ተቋቁሟል የተባለው ብሔራዊ ዐቢይ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የራያ ወሎ ዐማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በበኩሉ፣ “የብሔራዊ ኮሚቴው መግለጫ መሬት ላይ ያለውን እውነት ያገናዘበ አይደለም፤” በሚል ውሳኔውን ተቃውሞታል፡፡