በድርድሩ ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ተስፋ ያሳደሩ ተፈናቃዮች “ባለመሳካቱ አዝነናል” አሉ

የዐማራ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የአድቮኬሲ ወይም የሙግት ሥራ ክፍል ዲሬክተር አቶ ኾነ ማንደፍሮ፣ የኦሮሞ ውርስ አመራር እና ተሟጋች ማኅበር አባል ዶር. ጀማል ኢበኑ

የዐማራ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የአድቮኬሲ ወይም የሙግት ሥራ ክፍል ዲሬክተር አቶ ኾነ ማንደፍሮ፣ የኦሮሞ ውርስ አመራር እና ተሟጋች ማኅበር አባል ዶር. ጀማል ኢበኑ

ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በዐማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ የታንዛኒያው የመንግሥት እና የታጣቂው ቡድን የሰላም ድርድር፣ ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት እንደሚደረስበት ተስፋ ጥለውበት እንደነበር ገልጸው፣ ባለመሳካቱ ማዘናቸውን ተናገሩ፡፡

ተደራዳሪዎቹ፣ በጦርነቱ እየተሠቃየ ላለው ሕዝብ ሲባል ስምምነት ሊፈጥሩ ይገባ እንደነበር ያነሡት፣ የኦሮሞ ውርስ አመራር እና ተሟጋች ማኅበር አባል ዶር. ጀማል ኢበኑ ደግሞ፣ ድርድሩ ከመጀመርያውም የግልጽነት ችግር እንደነበረበት ይተቻሉ፡፡ ይኹንና፣ ሁለቱም ወገኖች ድርድሩን ቀጥለው፣ የሕዝቡን ሥቃይ ለማስቆም የሚያስችል የሰላም ውል መቋጠር እንደሚጠበቅባቸው፣ ዶር. ጀማል ያሳስባሉ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በድርድሩ ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ተስፋ ያሳደሩ ተፈናቃዮች “ባለመሳካቱ አዝነናል” አሉ

የዐማራ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የአድቮኬሲ ወይም የሙግት ሥራ ክፍል ዲሬክተር አቶ ኾነ ማንደፍሮ በአንጻሩ፣ ድርድሩ፥ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የዐማራ ተወላጆችን ሞት እና መፈናቀል ያስቆማል፤ የሚል እምነት የላቸውም፡፡ ችግሩን ለመፍታት ከተናጥል ድርድር ይልቅ የሚያስፈልገው ሃገር አቀፍ መፍትሄ ነው ይላሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።