Your browser doesn’t support HTML5
በጎሮ ዶላ ወረዳ ለዓመት የተቋረጠዉ ትምህርት ቢጀመርም 49 ትምህርት ቤቶች መውደማቸው ተነገረ
የምስራቅ ቦረና ዞን መመስረትን ተከትሎ በተቀሰቀሰዉ ተቃውሞ በጎሮ ዶላ ወረዳ ላለፈው አንድ ዓመት ሙሉ ተቁዋርጦ የነበረው ትምህርት ዘንድሮ መጀመሩን ነዋሪዎች እና የወረዳው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱ በአባ ገዳዎች ሽምግልና እንደተጀመረ የተነገረ ሲሆን፣ ያለፈው ዓመት ያለአገልግሎት የቆዩት 49 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸውን የወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ገልፆአል።