ምዕራብ ጎንደር ውስጥ ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት ወደ ሱዳን ተሰደው የቆዩ 838 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመላሳቸው ተገለጸ፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
ካርቱም የሚገኝው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ኤምባሲና የገዳሪፍ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ከሱዳን የስደተኞች ኮሚሽንና ከመንግስታቱ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር ስደተኞቹ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸውን የአትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
500 ያህል በሱዳን የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ቀሪ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡