በጎንደር ዩኒቨርሲቲ 102 ተማሪዎች ታሰሩ ተባለ

ጎንደር ዩኒቨርስቲ

ጎንደር ዩኒቨርስቲ

“የሥራ ዕድሉ በጣም ጠባብ ስለሆነ ዲፓርትመንት ይቀየርልን” ብለው የጠየቁ 102 የጎንደር ዩኒቨርስቲ የእንሳት ፈርማሲ ተማሪዎች ከትናንት በስቲያ አርብ መታሰራቸውን የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ዓመት ያሉ የእንስሳት ሕክምና ፈርማሲ ትምሕርት ክፍል ተማሪዎች ከእነርሱ ቀድመው የተመረቁ ተማሪዎች ሥራ ማግኘት ስላልቻሉ የትምህርት ክፍላቸው እንዲቀየር መጠየቅ ከጀመሩ ሦስት ሳምንት እንዳለፋቸው ለአሜሪካ ድምጽ የገለጸ ስሙን መናገር ያልፈለገ ተማሪ ይናገራል።

በዩኒቨርስቲው ውስጥ ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተል እንደነበር የገለፀው ይኸው ተማሪ ተማሪዎቹ መማር ካልፈለጉ ክሊራንስ ሞልተው ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስታወቂያ መለጠፉንና በዚህ መሰረት ክሊራንስ ሊሞሉ ሲሄዱ ተሰብስበው እንደታሰሩ ተማሪው ተናግሯል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝዳንት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋየል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ 102 ተማሪዎች ታሰሩ ተባለ