የጥምቀት በዓል ሰሞን፣ በቱሪዝም እና ተያያዥ ዘርፎች ለተሠማሩ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች፣ ጠቀም ያለ ገቢ የሚያገኙበት ቢኾንም፣ ዘንድሮ ግን የደንበኞቻቸው ቁጥር በእጅጉ እንደቀነሰና ገቢያቸውም እንደተቀዛቀዘ ገልጸዋል።
የአገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎች ብዛት በወቅቱ የጸጥታ ስጋት የተነሣ መቀነሱ፣ ለገቢያቸው ማነስ ምክንያት እንደኾነ፣ በአስጎብኝነት፣ በታክሲ ሥራ እና በሌሎችም የአገልግሎት ሰጪ ዘርፎች ላይ የተሠማሩ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር በአንጻሩ፣ በዘንድሮውም ክብረ በዓል የተገኙ ተሳታፊዎች ቁጥር በርካታ እንደኾነ ገልጾ፣ አኃዛዊ መረጃውን ከተገኘው ገቢ ጋራ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡