በድጋሚ የታደሰ
Your browser doesn’t support HTML5
በጎንደር ከተማ ባለፈው አርብ ባልታወቁ ሰዎች ታግታ ከተወሰደች በኋላ ግማሽ ሚልየን ብር ተጠይቆባት የነበረችው የ2 አመት ህፃን በትላንትው እለት መገደሏ ከተሰማ ወዲህ በከተማው ነዋሪዎች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡
አጋቾቹ ህፃኗን የገደሏት ወላጆቿ በድርድር እንዲከፍሉ የጠየቁትን 300 ሺ ብር ከተቀበሉ በኋላ ነው:: ዜናውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን አሰምተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በተደጋጋሚ እገታ በሚፈጸምባቸው አካባቢዎች የወንጀል ድርጊቱን ለመከላከል የሚያስችል የመንግስት የጥበቃና ቁጥጥር ሥራ ተግባራዊ እንዲሆን እና እንዲሁም የታጋቾች ደኅንነት እንዲረጋገጥ አሳስበዋል፡፡